Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተች መሆኗን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስለር ሚኒስትር ያንግ ይሃንግ ገለጹ።

የቻይና አፍሪካ የትብብር ኮንፈረንስ (ፎካክ) የከፍተኛ ባለሙያዎች ኮንፈረንስ “ኢትዮጵያ እንደ አፍሪካዊ ወካይ ድምጽ የነበራት ሚና ከትናንት እስከ ዛሬ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚሁ ወቅትም ጥምረቱ በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ አጋርነት መሆኑን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን÷ ኢትዮጵያ በፎካክ ውስጥ ግንኙነቱ እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋጻኦ እያበረከተች እንደምትገኝ አስረድተዋል፡፡

ያንግ ይሃንግ በበኩላቸው በተለይ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለው የንግድ እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን አመላክተው÷ በኢትዮጵያ የሚመረቱ በተለይም የግብርና ምርቶች በቻይና ገበያ ያላቸው ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ ወሳኝነት ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው÷ ባለፉት 24 ዓመታትም የፎካክ የትብብር ማዕቀፍ በአፍሪካ-ቻይና መካከል በማኅበረ-ኢኮኖሚ ዘርፎች ስኬት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ይህም በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ በድህንነት ቅነሳ እና ዲፕሎማሲያዊ ዘርፍ ሥራዎች ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው ያመላከቱት፡፡

በኮንፍረንሱ ላይ ፎካክን የተመለከቱ ሰባት የመነሻ ጽሑፎች ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.