Fana: At a Speed of Life!

በቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮችን በመለየት እየተሰራ ነው ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ዘርፉ ለሀገር ብልፅግና ያለውን ቁልፍ ሚና እንዲጫወት የሚያስችሉ የትኩረት መስኮችን በመለየት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቱሪዝም ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያዳመጠ ነው፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅቱ እንዳሉት፤ የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብቶች እንዲጠበቁ በጥናት በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ምቹ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲስፋፉ ተደርጓል።

እንዲሁም መስህቦችና መዳረሻዎች እንዲተዋወቁ መደረጉን ሚኒስትሯ መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሀገሪቱ የቱሪስት ፍሰትም ሆነ ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ እንዲያድግ እንዲሁም የመዳረሻ አካባቢ ማህበረሰቦች የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ ዘርፉ የተጣለበትን ተልዕኮ ለማሳካት እየሰራ እንደሚገኝም በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡

ተቋማዊ አቅምን ማሳደግ፣ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀምን ማጐልበት፣ የቱሪዝም መዳረሻና ምርት ልማት ስራዎችን ማጠናከር፣ የቱሪዝም ገበያ ልማት ስራዎችን ማስፋፋትና የቱሪስት አገልግሎት ጥራትን ማሳደግ የሚችሉ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት ወደ ሥራ መገባቱንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.