Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት መሪ ፕላን ረቂቅ ላይ እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት መሪ ፕላን ረቂቅ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የ10 ዓመት እቅዱ እስከ 2022 ዓ.ም ለመከናወን የታቀደ ሲሆን፥ የፖሊሲና ስትራቴጂ ፣ ያለፉት አመታት አፈጻጸምና የዓለም አቀፍና ከባቢያዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም ግቦችን መሠረት በማድረግ የታቀደ ነው።

በእቅዱ የሠብአዊ ልማት፣ ፈርጀ ብዙ የድህነት መለኪያ እንዲሁም የዜጎች በኑሯቸው ያላቸው እርካታ የብልጽግናን ደረጃ ለመለካት የሚያገለግሉ አመላካቾች መሆናቸውም በውይይቱ ተጠቁሟል።

የአለም አቀፍ የልማት ግቦችን እና የአፍሪካን የአጀንዳ 2063 ግቦችን ታሣቢ ያደረገ ሲሆን፥ እቅዱ የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ መሪነትን ጨምሮ በ6 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አሉት፡፡

በዚህም በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ይተገበራል በተባለው መሪ እቅድ የአገሪቷ አመታዊ አማካይ የኢኮኖሚ ዕድገት 10 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚሆን እና የግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ ከተማ ልማት፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ በእቅዱ ትኩረት የተሰጣቸው ዘርፎች ናቸው፡፡

ከሀገራዊው እቅድ ጎን ለጎንም የአዲስ አበባ ከተማ የ10 አመት መሪ እቅድ መዘጋጀቱን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.