Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት 2ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ጥላሁን በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር በክልሉ እየታየ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ማስጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ጠቅሰው÷ ሕዝቡም በሰላም ላይ በትጋት መሥራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

ሰላሟ የተጠበቀ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ለመገንባት በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡

ከሕዝቡ በተጨማሪ የፀጥታ አካላት የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ እና ሰላምን በማስፈን ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በማስተዋል አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.