Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል 227 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 227 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ÷ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች በመተካት እና ወጪ ንግድን በመደገፍ የውጪ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው 2 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ጠቁመው÷ በዚህም 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ማዳን መቻሉን አንስተዋል፡፡

10 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት በማቅረብ የጨርቃ ጨርቅ፣ ምግብና – ብረታ ብረት ፣ የቆዳና ሌጦ ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

107 ሺህ ቶን ምርቶች ወደ ውጪ ሀገራት ተልከው 202 ሚሊየን ዶላር እንደተገኘም ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት ተናግረዋል፡፡

20 ቢሊየን ብር ግምት ያለው የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ እንተቻለ መናገራቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ክልሎች ሰላምና ጸጥታን በማስጠበቅ እራሳቸውን ለኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ማሳደግ እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.