Fana: At a Speed of Life!

በሲንጋፖር የመንገጫገጭ አደጋ ያጋጠመው አውሮፕላን መንገደኞች 20ዎቹ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲንጋፖር በበረራ ወቅት ከባድ የመንገጫገጭ አደጋ ያጋጠመው አውሮፕላን መንገደኞች መካከል 20ዎቹ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ተነገረ።

አውሮፕላኑ በሲንጋፖር ቻንጊ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲደርስ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፥ እስከአሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በተከሰተ መንገጫገጭ በምትኩ ታይላንድ ማረፉ ተነግሯል፡፡

በዚህም 20 መንገደኞች በሁለት የባንኮክ ሆስፒታሎች ውስጥ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ የሆስፒታሎቹ የሥራ ኃላፊዎች የተናገሩት፡፡

ክስተቱ ካጋጠመ በኋላም አንድ የ73 ዓመት ሰው ህይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፥ የሲንጋፖር አየር መንገድ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

ሌሎች ሠላሳ ስድስት ተሳፋሪዎች በሆስፒታሎቹ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተገለጸ ሲሆን፥ 27 ሰዎች ከሆስፒታል መውጣታቸውም ተነግሯል፡፡

አየር መንገዱ በዚህ ወቅት፥ በአውሮፕላኑ ውስጥ ለነበሩ መንገደኞችና ሰራተኞች እርዳታ ማድረግ ቅድሚያ የምሰጠው ጉዳዬ ነው ብሏል፡፡

ቦይንግ 777-300ኢአር አውሮፕላን 221 መንገደኞችን እና 18 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ትናንት ከለንደን ሄትሮው አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ እንደነበር የዘገበው ኤቢሲ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.