Fana: At a Speed of Life!

በ85 ሚሊየን ብር የሚገነባው የሃላባ በሽኖ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በሃላባ ዞን፡ የሃላባ በሽኖ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የፌደራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተቀመጠ።
 
ፕሮጀክቱ ድርቅ በተደጋጋሚ በሚያጠቃባቸውና የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ከሚከናውነት የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ሥራዎች አንዱ ነው፡፡
 
85 ሚሊየን ብር የሚፈጀው ፕሮጀክቱ በ14 ቀቤሊያት የሚገኙ 59 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የውሃ መስናኖና ኢነርጂ ሚኔስቴር አስታውቋል።
 
ወጪዉም ሙሉ በሙሉ በፈዴራል መንግሥት የሚሸፈን ሲሆን ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን በሌሎች ክልልችም ለማስጀመር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል ተብሏል፡፡
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.