በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና ጨፌ ኦሮሚያ የኦሮሚያ ተወካይ ሴቶች የሰላም ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ክልልን ወክለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ጨፌ ኦሮሚያ የሚገኙ ሴት አባላት የሰላም ጥሪ አቀረቡ።
የሰላም ጥሪው የቀረበው በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ታጣቂዎች ሲሆን÷ ታጣቂዎቹ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እናቶች ስንቄያቸውን በመያዝ ጠይቀዋል፡፡
የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሚመጡ ታጣቂዎች ለመቀበል መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ሰዓዳ አብድረህማን አረጋግጠዋል፡፡
በሀገር እድገት እና ብልፅግና ላይ በመሳተፍ እንደዜጋ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም አስገንዝበዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ