Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ሳዑዲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የኢትዮ-ሳዑዲ ዓረቢያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ትናንትናና ዛሬ በሪያድ ተካሂዷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሳዑዲ ዓረቢያ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የጸና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነቶች መፈራረማቸውን በመግለጽ÷ የአሁኑየጋራ ኮሚሽን ስብሰባም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ልዩ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡

ከሳዑዲ ዓረቢያ የአካባቢ፣ ውኃ እና ግብርና ሚኒስትር አብዱረህማን አል አልፋደሊ (ኢ/ር)በበኩላቸው÷ ሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ የእንስሳት ሀብት ልማት ላይ ለመስራት እና በኢንቨስትመንትና ንግድ ዘርፎችያላቸውን ተሳትፎ በግል ባለሃብቶች ጭምር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

ከጋራ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ቀደም ብሎ በተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ÷ በፖለቲካዊ፣ ጸጥታ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊጉዳዮች ላይ በዝርዝር በመምከር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በስብሰባው መጨረሻም በወጪና ገቢ ንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በሪልስቴት፣ በእንስሳት ሀብት፣ በግብርና እና አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በመሰረተ-ልማት፣ በማዕድን ዘርፎች፣ በሰላምና ደኅንነት እንዲሁም በኃይል አማራጭ፣ በሰው ሀብት ስራ ስምሪት ዘርፎች ከመንግስትና ከግል ባለሀብቶች ጋር በትብብር በመስራት የሀገራቱን ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል የስምምነት ቃለ-ጉባዔ ተፈራርመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.