Fana: At a Speed of Life!

ማዳበሪያን በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ርብርቡ እንዲጠናከር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት አፕሬተሮች የአፈር ማዳበሪያን በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሥራቸውን በትጋት እንዲቀጥሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጠየቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሥራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ከትራንስፖርት ኦፕሬተሮች ጋር ገምግሟል።

በመድረኩም ከኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ጋር ውል ይዘው የአፈር ማዳበሪያን ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች እያጓጓዙ ያሉ ኦፕሬተሮች አፈፃጸም ሪፖርት ውይይት ተደርጐበታል::

በሪፖርቱም በርካታ ኦፕሬተሮች በውላቸው መሠረት በብቃት ሥራቸውን ሲያከናውኑ በአንፃሩ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ኦፐሬተሮች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡

የማደበሪያ ማጓጓዝ ስራ በመንግሥት ከፍተኛ ክትትል የሚደረግበትና በየጊዜው እየተገመገመ የሚፈፀም መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ ዴንጌ ቦሩ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡

ወቅቱ ሙሉ አቅም በመጠቀም መስራትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው፤ ሁሉም ኦፕሬተሮች ማዳበሪያን በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ በከፍተኛ ርብርብ እንዲሠሩ ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.