Fana: At a Speed of Life!

አዋሬ ያላሰለሰ ጥረት የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤና ተስፋ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ምልክት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)አዋሬ ያላሰለሰ ጥረት የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤና ተስፋ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ምልክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ “ዛሬ በአዋሬ አካባቢ ከስድስት አመታት በፊት በጀመርነው የዝቅተኛ ወጪ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅስቃሴ ምናልባትም የመጨረሻው ስፍራውን ለግንባታ ዝግጁ የማድረግ ስራ ተሰርቷል” ብለዋል።

የመኖሪያ ሁኔታዎቹ ችግር የበዛባቸው ነበሩ፤ እጅግ ያረጁ፣ የተጠባበቁ፣ መፀዳጃ የሌላቸው መኖሪያዎች ነበሩ ሲሉ ጠቅሰዋል።

ምቹ የመኖሪያ እና አረንጓዴ አካባቢ የሚያካትተው አዲሱን የመኖሪያ ህንፃ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር ለማጠናቀቅ ዛሬ ማስጀመራቸውን ገልጸው፤ ይህ ስራ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ወገኖችን ህይወት ብቻ ሳይሆን የሪል ስቴት አልሚዎችንም የጠቀመ ነው ብለዋል።

በዚህ ፕሮጀክት የቀጣይነት መንፈስ አይተንበታል፤ አፅንተንበታልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትርሩ፤ አዋሬ ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ጥረት የመኖሪያ አካባቢዎችን ሊለውጥ የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ እና ተስፋ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ምልክት ነው ሲሉም ገልፀዋል።

የዚህ አመቱ የዝቅተኛ ቤቶች ግንባታ ወጪ በከፊል በቪዛ ፋውንዴሽን መሸፈኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊዎች ለዜጎች ህይወት እና ከባቢ መለወጥ ያለመታከት ልግስናቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.