Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ባለፉት 10 ወራት ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አወል አብዱ እንደተናገሩት÷ በክልሉ የገቢ አማራጮችን በማስፋት የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በኢኮኖሚው ዘርፍ በሀገሪቱ ላይ እየተደረገ ያለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የገቢ አቅምን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ክልሉ የድርሻውን ለመወጣት የገቢ አማራጮችን በመጠቀም ለመሰብሰብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ባለፉት 10 ወራት ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ እንደተሰበሰበ መጥቀሳቸውንም የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.