Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢፌዲሪ ሚሲዮኖች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው ባሉ ስራዎች ላይ ከኢፌዲሪ ሚሲዮኖች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ ላይ ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ተግባራት፣ ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና ዳያስፖራውን በምክክር ሂደቱ ከማሳተፍ አንጻር ከኢፌዲሪ ሚሲዮኖች በሚፈልጋቸው ትብብሮች ላይ ገለጻ ቀርቧል።

በወቅቱ የሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነትና ምክክር ግጭቶችን በማስወገድ ረገድ ያለው ሚናም ተብራርቷል ነው የተባለው።

ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላትና አደረጃጀቶች ጋር በመገናኘት ውይይት ማድረጉና ከውይይቶቹም ጠቃሚ ግብአቶችን ማሰባሰብ መቻሉም ተጠቅሷል።

በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ዳያስፖራው የሚኖረውን ሚና ለማሳደግም የሚደረጉ ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በመድረኩ ሀገራዊ ምክክሩ ከግጭት አዙሪት ለመውጣት የሚያገለግልና በተደጋጋሚ የማይገኝ ዕድል በመሆኑ በጥንቃቄ ሊመራ እንዲሁም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተነስቷል፡፡

ኮሚሽነሮች በበኩላቸው ፥ በምክክር ሂደቱ ውስጥ ሁሉንም የሀገሪቱን ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የዳያስፖራ አካላትን ለማካተት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም የምክክር ሂደቱን በስኬት በማጠናቀቅ ለሁላችንም የምትመች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እንሰራለን ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.