Fana: At a Speed of Life!

በሜክሲኮ በተከሰተ የመድረክ መደርመስ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሜክሲኮ በተከሰተ የመድረክ መደርመስ አደጋ አንድ ህፃንን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ህወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡

አደጋው የሜክሲኮ ሴንተሪሰት ሲቲዝንስ ንቅናቄ ፓርቲ መሪ ጆርጌ አልቫሬዝ ሜኔዝ በኒኦቮ ሊዮን ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት መከሰቱ ነው የተገለፀው፡፡

በአደጋው ከደረሰው የሞት ጉዳት በተጨማሪ ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረውን ፓርቲ መሪ ጨምሮ 50 ያህል ሰዎች መጎዳታቸው ተገልጿል፡፡

ሚስተር ሜኔዝ ከአደጋው በኋላ በሳን ፔድሮ ጋርዛ ከተማ ወደሚገኘው ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በአደጋው አሁንም ከፍርስራሹ ውስጥ ያልወጡ ሰዎች መኖራቸው እና የሟቾች ቁጥርም ሊጨመር እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

እጩ ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክትም÷ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ለመንከባከብ ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ የምርጫ ቅስቀሳው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አስታውቀዋል።

የኒኦቮ ሊዮን ግዛት አስተዳዳሪ ሳሙኤል ጋርሺያ÷ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት የነበረው ነፋስ የተቀላለበት ዝናብ ለአደጋው ምክንያት ነው ማለታቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.