Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገልግሎት ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጪ ቆጣቢ የትራንስፖርት ስርዓት ለመፍጠር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በማራቶን ሞተርስ 15ኛ ዓመት የመመስረቻ በዓል ላይ እንዳሉት÷ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በመቀነስ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገልግሎት ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ማራቶን ሞተርስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለአየር ንብረት የማይበገር የትራንስፖርት ዘርፍ ለመገንባት የሚደረገውን የመንግስት እንቅስቃሴ በመቀላቀል እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንደሀገር በታዳሽ ሃይል ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ትኩረት በመስጠት የዓለም ስጋት እየሆነ የመጣውን የአየር ብክለት መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ ያለውን እምቅ ሃብት በመጠቀም ራስን መቻልና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከብክነት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንትንና አስመጪዎችን የሚያበረታታ እንዲሁም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታክስ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደርጓል ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የማራቶን ሞተርስ መስራችና ሊቀ-መንበር አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ብረስለሴ በበኩሉ÷ ባለፉት 15 ዓመታት በብዙ ፈተና ውስጥ የተመዘገበው ውጤት ሀገር የሚያኮራ መሆኑን አንስቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.