Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 368 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 232 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም በከተማዋ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 368 መድረሱን ነው የከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሪፓርት ያመለከተው።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በ24 ሰዓታት ውስጥ በአዲስ አበባ 8 የኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 28 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.