Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ሚኒስቴሩ አሁን ላይ የሀገሪቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፍላጐት ለማሟላት የየብስ፣ የዓየርና የባህር ትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማሳለጥ እየሰራቸው የሚገኙ ተግባራትን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ከሪፎርሙ በኋላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደረሰበት ደረጃ እና ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ሆኖም ግን በሚኒስቴሩ አሁንም ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ መዘግየት፣ ለተገልጋይ ምቹ ከባቢ የመገንባትና በቅርብ የአመራር ድጋፍ ለመስጠት የሥራ ከባቢው መራራቅ ፈጥነው ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ተግባብተናል ነው ያሉት፡፡

በቀጣይ ሚኒስቴሩ ያሉበትን ለተገልጋይ ምቹ የሥራ ከባቢ የመገንባት ማነቆዎች ተወያይተን በጋራ ለመፍታት አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.