Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የዜጎች ተሳትፎ (ኢ ኤፍ ፒ) መተግበሪያን አስጀመሩ

አዲሰ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ (ኢ ኤፍ ፒ) መተግበሪያን በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (ኢ ኤፍ ፒ) አስጀምሯል ብለዋል።

ይህ ሥራ ለዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ የሚከናወነው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የሁሉንም ዘርፎች ምሉዕ አቅም ለማሳካት በዲጂታል ኢትዮጵያ መደገፍ እንዳለባቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ስርዓት መሸጋገሩን ገልጸዋል።

የህዝብ ብዛት እየጨመረ ባለበት ከተማችን ንቁ የዜጎች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፥ ዛሬ ወደስራ የገባው መተግበሪያ በአፕ ስቶር እና ፕለይስቶር እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

መተግበሪያው ዜጎች ወንጀልን ለመከላከል በፎቶ ግራፍ፣ በቪዲዮ፣ በድምፅ፣ በሰነድ ወይም በቀጥታ በመደወል ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ዜጋ የአካባቢውንና ከተሞችን ደህንነት ለማስጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.