Fana: At a Speed of Life!

ቢኒያም ዳዊት (ፕ/ር) የተመድ የሕጻናት መብቶች ኮሚቴ አባል ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቢኒያም ዳዊት (ፕ/ር) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሕጻናት መብቶች ኮሚቴ አባል ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።

ቢኒያም ዳዊት (ፕ/ር) የተመድ የሕጻናት መብቶች ኮሚቴ አባል ሀገራት ዛሬ በኒውዮርክ ባካሄዱት ስብሰባ ነው በድጋሚ በአባልነት የተመረጡት፡፡

ቢኒያም (ፕ/ር) የኮሚቴው ነባር አባል ሲሆኑ÷በሊቀ-መንበርነት ማገልገላቸውንም በተመድ የኢትዮጵያ ተወካይ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.