Fana: At a Speed of Life!

የሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የዲጂታል ሥርዓትን ከውጤት ለማድረስ ወሳኝ ናቸው – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች መንግሥት የጀመረውን የዲጂታል ሥርዓት ዕውን የማድረግ ጉዞ ከውጤት ለማድረስ ወሳኝ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።

“ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርምሮችን ማምጣት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት 3ኛው ብሔራዊ የምርምር ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው፡፡

ሚኒስትሩ በሲምፖዚየሙ ላይ ባደረጉት ንንግር÷ የሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች መንግሥት የጀመረውን የዲጂታል ሥርዓት ዕውን የማድረግ ጉዞ ከውጤት ለማድረስ ወሳኝ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የዲጂታል መስመሩን መከተል ወሳኝ መሆኑን ገልጸው÷ እንደዚህ ያሉ የቴክኖሎጂ ምርምር ሲምፖሲየሞችም የሣይንሳዊ ዕውቀትን የበለጠ ለማዳበር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የምርምርና የጥናት ውጤቶች የዜጋን ችግር የሚፈቱ እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በተግባር የሚያሳዩ ሊሆኑ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በተለይም አሁን ዓለም የደረሰበትን የዲጂታል ሥርዓት ለመተግበር በዚህ መስመር መጓዝ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.