Fana: At a Speed of Life!

ሪያል ማድሪድ፣ ማንቼስተር ዩናይትድና ባርሴሎና ውድ ክለቦች ተባሉ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሪያል ማድሪድ፣ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ባርሴሎና የወቅቱ ውድ ክለቦች በመባል ተመረጡ፡፡

የአሜሪካው የቢዝነስ ጋዜጣ ፎርብስ የ2024 ውድ ክለቦችን ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን ሪያል ማድሪድ፣ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ባርሴሎና ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ አመታት ብቻ አምስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮን መሆን የቻለው የስፔኑ ሪያል ማድሪድ አሁን ላይ በ6 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ የዓለማችን ውድ የእግር ኳስ ክለብ ብራንድ መሆን ችሏል፡፡

ከሪያል ማድሪድ በመቀጠል የእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ በ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል።

ማንቼስተር ዩናይትድ በ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመንን 8ኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅም ከብሪታኒያ ክለቦች መካከል ውድ ዋጋ ያለው ክለብ በሚል በቀዳሚነት ተቀምጧል።

የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና በ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ግምት ሶስተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ሊቨርፑል በ5 ነጥብ 3፣ ማንቼስተር ሲቲ በ5 ነጥብ 1፣ ባየርን ሙኒክ በ5፣ ፒ ኤስ ጂ በ4 ነጥብ 4፣ ቶተንሃም በ4 ነጥበ 2፣ ቼልሲ በ3 ነጥብ 1፣ አርሰናል በ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር እስከ 10ኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.