Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሮም የአበበ ቢቂላን ምስለ-ቅርጽ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የኢትዮጵያ የመከላከያ ልዑክ በሮም የሚገኘውን የአትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ምስለ-ቅርጽን ጎበኘ፡፡

በላቀ የሥነ-ጥበብ ይዘት የተሠራው የአበበ ቢቂላ ምስለ-ቅርጽ በፈረንጆቹ ሐምሌ 23 ቀን 2023 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መቀመጡ ይታወሳል፡፡

ይህም ጎብኝዎች የአትሌቱን ታሪክ ግልጽና ቀላል በሆነ ሁኔታ ዐይተው እንዲረዱት በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው መባሉን በጣልያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ኢትዮጵያን ከፍ ከማድረግ ባሻገር ከጣልያን ጋር ያላት ግንኙነት በጥብቅ እንዲተሳሰር ማስቻሉም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.