Fana: At a Speed of Life!

ለቤላሩስ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እድሎች ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ሞስኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እድሎች ለቤላሩስ ባለሀብቶች ገለጻ አደረገ፡፡

ኤምባሲው ከቤላሩስ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በቤላሩስ ዋና ከተማ ሚኒስክ የቢዝነስ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ በግብርና፣ ማምረቻ ዘርፍ፣ መድሀኒት ማምረት እና አይሲቲ ዘርፎች የተሰማሩ ከ55 በላይ ኩባንያዎችና የንግድ ድርጅቶች ተሳትፈዋል።

ኤምባሲዉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እድሎች እንዲሁም ማበረታቻዎች ላይ ገለፃ ማድረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የኤምባሲዉ የልዑካን ቡድን ከቤላሩስ ብሔራዊ የኢንቨስትመንት እና ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዲሚትሪ ክራስቭስኪ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.