Fana: At a Speed of Life!

ሃንሲ ፍሊክ የባርሴሎና አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ የባርሴሎና አሰልጣኝ ለመሆን በቃል ደረጃ መስማማታቸው ተገለፀ፡፡

የ59 ዓመቱ አሰልጣኝ ከሰዓታት በፊት የተባረረውን ዣቢ በመተካት ነው የካታሎኖን ክለብ ለመረከብ የተስማሙት፡፡

ፍሊክ በሁለት ዓመት ኮንትራት ክለቡን በአሰልጣኝነት ለመረከብ መስማማታቸው  የተገለፀ ሲሆን÷ አሰልጣኙ  ሁለት ረዳት አሰልጣኞችን ከጀርመን ለማምጣትም ከባርሴሎና ጋር መስማማታቸው  ተገልጿል፡፡

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ ቀደም ሲል ባየርን ሙኒክን እና ኤፍ ፍሲ ኮልኝን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.