Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ናሽናል ከተሰኘ ሀገር በቀል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር የአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት÷ ስምምነቱ ለኢትዮጵያን ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።

በተጨማሪም በኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ እና ግብአቶች ማምረት ውስጥ ኢትዮጵያ ያላትን ተሳትፎ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የተፈረመው የ110 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን አካላትንና መለዋዎጫዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚያስችለው እንደሆነ ተነግሯል።

ናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሙሉ ለሙሉ ወደ ተግባር ሲገባ 1 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ሀገሪቱ ለአውሮፕላን አካላትንና መለዋወጫዎች የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀርና እቃዎቹን ወደ ሌሎች ሀገራት ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.