Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 183 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 183 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት ዜጎች መካከል ሴቶች እና ጨቅላ ህፃናትም ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ29 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.