Fana: At a Speed of Life!

የወጣቶች ድምጽ ለሀገራዊ ምክክር የግንዛቤ ማስጨበጫ የማህበራዊ ድህረ ገጽ ንቅናቄ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶችን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ ለማጠናከር የሚያስችል የማህበራዊ ድህረ ገጾች የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ይፋ ተደርጓል፡፡

የወጣቶች ድምጽ ለሀገራዊ ምክክር በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ንቅናቄ ወጣቶች በሀገራዊ ምክክሩ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ረገድ የመሪነት ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል።

በንቅናቄው ከተለያዩ ማህበራት የተወጣጡ ወጣቶች፣ በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች፣ በሚዲያና ፈጠራ ስራ የተሰማሩ ወጣቶችን እንደሚያሳትፍ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ አመልክቷል።

የንቅናቄ መድረኩ ለሶስት ወር የሚዘልቅ ሲሆን ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግ የታለመ መሆኑም ተነግሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.