Fana: At a Speed of Life!

ኦሮሚያ በሁሉም የቱሪስት መስኅቦች የበለፀገች ናት- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ በሁሉም የቱሪስት መስኅቦች የበለፀገች፤ የበርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ የሚያኮራ የታሪክ ቅርስና መካነ-ባህል ናት ሲሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልሽ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ዕንቁ ሀብቶች በሂደት በተለያዩ ምክንያቶች ችላ መባላቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ዛሬም የተፈጥሮ ሀብት መራቆት በግልጽ ይስተዋላል፤ በሌላ በኩል ከህዝቡ ትውፊት የመነጨ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ባህል አሁንም በህብረተሰቡ ዘንድ አልተረሳም ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ለዚህ ዋነኛው ምሳሌ የባሌ ህዝብ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፤ የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ህዝባችን ለአለም ካበረከታቸው ልዩ እና ውድ ስጦታዎች አንዱ ነው ብለዋል።

መንግስት ለጉዳዩ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ባህል መልሶ እያቆጠቆጠ መሆኑን አመላክተው፤ ህዝባችን የተፈጥሮ ሀብት ውድመትን የሚያስቆም የውጭ አካል እንደሌለ ተረድቶ የተፈጥሮ ሀብት ጠበቃና ጠባቂ እየሆነ ነው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

መንግስት በበኩሉ ለዚህ ዘርፍ ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነቱን እየተወጣ፣ ለህብረተሰባችን የሚጠቅሙ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ውጤታማ በማድረግ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።

በዚህ ረገድ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማስቀጠልና የህዝባችንን ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ ሁሉም እንዲተባበር አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.