Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ በባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ የጉብኝታቸው አንድ አካል የሆነውንና በቅርቡ ተመርቆ በይፋ ሥራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀውን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱም ሆስፒታሉ አገልግሎት ለመጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

ሆስፒታሉ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከ 7 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ይጠበቃል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.