Fana: At a Speed of Life!

የአደረጃጀት ሪፎርሙ መንግሥት ዴሞክራሲን ማሳለጥ ግቡ መሆኑን ያሳያል-  አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ በባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው የአደረጃጀት ሪፎርም ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን ማሳለጥ ዋነኛ ግቡ መሆኑን ያመላክታል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ተናገሩ።

የምሥራቅ ጉራጌ የልማት፣ የምስረታና ኢንቨስትመንት ፎረም በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል፡፡
አቶ እንዳሻው በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ክልሉን ጨምሮ ሌሎች የተመሰረቱ አደረጃጀቶች የፖለቲካዊ አሥተዳደር መዋቅርን ለሕዝብ ቅርብ ለማድረግ ያለሙ መሆናቸውን አስገንዝበዋ፡፡

የአብሮነት ዕሴቶችን እና መስተጋብሮችን በይበልጥ በማጠናከር የጋራ ትርክት ለመፍጠር  ሊሰራ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

የተመሰረቱ አደረጃጀቶች ለሕዝቡ ተጨማሪ ልማትና ዕድገት እንዲያመጡ ልንጠቀምባቸው ይገባል ብለዋል።

የምሥራቅ ጉራጌ ዞንን የመልማት አቅም ለማሳደግም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የዞኑ ተወላጆችና ወዳጆች፣ የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም የግል ድርጅቶች 425 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በኤርሚያስ ቦጋለ፣ ጥላሁን ይልማ እና ጀማል ከዲሮ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.