Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ እርምጃዎች ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የያዘውን ቁርጠኝነት ያመላክታል – አቶ መለሰ ዓለሙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል እንዲለወጥ እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎችና እየተገኙ ያሉ ውጤቶች ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የያዘውን ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ መሆኑን የፓርቲው የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለሰ ዓለሙ ገለጹ።

ኃላፊው መለሰ ዓለሙ÷ፓርቲው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ በርካታ እርምጃዎች መውሰዱን ገልጸዋል።

የመንግስት ስልጣን ሽግግር በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲሆንና 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያከናወነው ስራ ለዴሞክራሲ ባህል መዳበር አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

ፓርቲው የዴሞክራሲ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩና ዜጎች በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድም ውጤታማ ስራዎችን መከናወናቸውን አስረድተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቋማዊና ሎጅስቲካዊ አቅም እንዲጠናከር በማድረግ የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብትና የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ ከፓርቲዎቹ ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው ያሉት ኃላፊው።

ብልጽግና ፓርቲ ለችግሮች መፍትሄ የሚገኘው በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግል ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጸው፤ በኃይል የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የሚደረግ ጥረት ኢትዮጵያና ሕዝቧቿን አይመጥንም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ማንኛውም ጉዳይ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይትና በሀሳብ የበላይነት ይፈታል ብሎ እንደሚያምንም አብራርተዋል።

ፓርቲው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት የያዛቸውን አቋሞች በማጠናከር በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እንዲጎለብት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.