Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ጎጃምና አዊ ብሔረሰብ ኮማንድ ፖስት ከሠራዊቱ አመራሮች ጋር ተወያየ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ጎጃምና አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ከሠራዊቱ አመራሮች፣ ከክልል የጸጥታ ኃላፊዎችና ከፖለቲካ አመራሮች ጋር ተወያየ፡፡

በኮማንድ ፖስቱ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ኮር በዳንግላ ዙሪያ ከሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች የክልል የጸጥታ አካላት አመራሮች እና ከፖለቲካ አመራሮች ጋር ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እና የልማት ስራዎችን ያለ ጸጥታ ችግሮች ማከናወን የሚያስችል ውይይት ነው ያደረገው፡፡

የሰሜን ጎጃም ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢና የኮሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አዲሱ መሃመድ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ጽንፈኛው ቡድን የጥፋት አጀንዳውን ለማስፈፀም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ህዝቡ የጥፋት ቡድኑ ለግል ጥቅሙንና ሀብት ለማካበት እንጂ ለአማራ ህዝብ አለመቆሙንና ለህዝብ የሚጠቅም አጀንዳ እንደሌለው ተረድቷል፡፡

ከዚህ ቀደም በተሳሳተ ትርክትና በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ማህበረሰቡ የተዛባ አመለካከት እንዲይዝና ለጥፋት አጀንዳው ተባባሪ እንዲሆን በማድረግ ህዝቡን ሲያንገላታ መቆየቱንም መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተደረጉ የህዝብ ውይይቶች የማህበረሰቡ አመለካከትና እይታ ተቀይሯል፤ በዚህም ህዝቡ መረጃ በመስጠትና የጥፋት ቡድኑን በመጠቆም መልካም ትብብሮችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል ፡፡

ሰራዊቱ ከክልል የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ሁሉ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ጽንፈኛውን ከህዝብ ነጥሎ የመደምሰስ ተልዕኮውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አዛዡ አረጋግጠዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.