Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር ሀይል የአየር መንገዱን አብራሪዎችና ቴክኒሻኖች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ሀይል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎችና ቴክኒሻኖችን አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

በምረቃ መረሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሳው እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአየር ሀይል አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል፡፡

የአየር መንገዱ ሠልጣኞች በጠንካራ ስነ- ልቦና፣ በአካል ብቃት እና በፅኑ የሀገር ፍቅር ስሜት ሀገርንና ህዝብን ማገልገል የሚያስችል እውቀት የጨበጡ መሆናቸው መገለፁን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂ የእውቀት ሽግግር በጋራ መስራት የሚያስችላቸው ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.