Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ በተከናወኑ የሊጉ ጨዋታዎች መሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተከናወኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 1ለ 0 አሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን1ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ጎሎቹን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ግደይ ሲያስቆጥር ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥሯል፡፡

ሊጉን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ56 ነጥብ ሲመራ ፣መቻል በ51፣ ባህርዳ ር ከተማ በ45 ነጥብ ይከተላሉ፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.