Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ በማሸነፍ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ፡፡

በዌምብሌይ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሠዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቀያይ ሰይጣኖቹ ውኃ ሰማያዊዎቹን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

የዩናይትድን ጎሎች ግራናቾ እና ማይኖ ሲያስቆጥሩ የሲቲን ደግሞ ዶኩ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

የዛሬውን ጨምሮ ዩናይትድ 13 ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ሲያነሳ ሲቲ ደግሞ 7 ጊዜ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

አርሰናል የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን 14 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.