Fana: At a Speed of Life!

 የፓኪስታን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ልዑክ ኢትዮጵያ ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ80 በላይ አባላት ያለው የፓኪስታን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ልዑክ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩን የመሩት በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በክሪ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት የልዑክ ቡድኑን ተቀብለዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ልዑኩ በኢትዮጵያ በተለይም ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ግዙፍና ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ማዕከላት የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸውን ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በመጎብኘት በፋርማሲዩቲካል፣  በቴክስታይልና ጋርመንት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያሉ አማራጮችን ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ ለቅድመ ኢንቨስትመንት ትግበራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.