Fana: At a Speed of Life!

በዩጂን ዳይመንድ ሊግ ድርቤ ወልተጂ እና ጽጌ ገብረሰላማ  በተለያዩ እርቀቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩጂን ዳይመንድ ሊግ ድርቤ ወልተጂ በ 1 ሺህ 500 እና ጽጌ ገብረሰላማ በ5 ሺህ ሜትር ቀዳሚ በመሆን አሸነፉ።

በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች አትሌት ድርቤ ወልተጂ 3 ደቂቃ 53 ሴኮንድ ከ75 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡

በሌላ ርቀት የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ጎልቶ በታየበት 5 ሺህ ሜትር ሴቶች ፅጌ ገብረሰላማ 14 ደቂቃ 18 ሴኮንድ ከ76 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡

በዚህ ውድድር ጽጌ ገብረሰላማን በመከተል እጅጋየሁ ታዬ፣ ፍሬወይኒ ሃይሉ፣ አይናዲስ መብራቱ፣ ብርቄ ሃየሎም እና ሂሩት መሸሻ በቅደም ተከተል ከ2ኛ እስከ 6ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

10 ሺህ ሜትር ሴቶች ከፍተኛ ግምት አግኝታ የነበረችው ጉዳፍ ፀጋይ 29 ደቂቃ 05 ሴኮንድ ከ92 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.