Fana: At a Speed of Life!

የሁቲ አማጺያን ሁለት የፀረ መርከብ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ቀይ ባህር ማስወንጨፋቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን የሚንቀሳቀሱት የሁቲ አማጺያን ሁለት የፀረ መርከብ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ቀይ ባህር ማስወንጨፋቸውን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አስታወቀ፡፡

ሚሳኤሎቹ በአሜሪካ መራሹ ጥምር ሀይልም ሆነ በንግድ መርከቦች ላይ ጉዳት አለማድረሳቸውን ዕዙ ገልጿል።

የሁቲ አማጺያን ጥቃቶች የመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥል እና በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ያሉ መርከበኞችን ህይወት ስጋት ውስጥ የሚከት መሆኑንም አስገንዝቧል።

አማፂያኑ እስራኤል በጋዛ ዘመቻ ማድረግ ከጀመረችበት የፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ቀን 2023 ጀምሮ የእስራኤል፣ የአሜሪካ እና የተለያዩ ሀገራት ንብረት በሆኑ መርከቦች ላይ ጥቃት ሲፈፀሙ ቆይተዋል፡፡

የየመን የሁቲዎች መሪ አብዱል ማሊክ አል-ሁቲ÷ ወደ እስራኤል ወደቦች የሚያመሩ መርከቦች በሙሉ የቡድኑ የጥቃት ዒላማ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቁን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.