Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን ለዓለም አቀፍ የሐረር ቀን እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ከ26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

አቶ ኦርዲን በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በሐረር ከተማ መከበሩ የክልሉ የልማት ሥራዎች የበለጠ እንዲነቃቁ ከማድረግ አንፃር ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ መረባረብ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

ክብረ በዓሉን የተሳካ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎችን ማጎልበት እንደሚገባ መናገራቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሸን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.