Fana: At a Speed of Life!

ሃማስ በቴል አቪቭ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃማስ በማዕከላዊ እስራኤል ቴል አቪቭ አካባቢ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ አል ቃሲም ብርጌድ÷በዛሬው ዕለት በቴል አቪቭ አካባቢ“መጠነ ሰፊ” የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

ጥቃቱ እስራኤል በጋዛ እና ሌሎች አካባቢዎች እየፈጸችው ላለው ወታደራዊ ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ መሆኑን ገልጿል፡፡

የእስራኤል ጦር በበኩሉ÷በደቡባዊ ጋዛ ራፋ አካባቢ ቢያንስ 8 ሮኬቶች ተመትተው መውደቃቸውን እና በርካቶች ግባቸውን ሳይመቱ መምከናቸውን አስታውቋል፡፡

ሄርዝሊያ እና ፔታህ ቲክቫን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የሮኬት የአደጋ ጊዜ ጥሪ ሲሰማ እንደነበርም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

በጥቃቱ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ የተገለጸ ሲሆን÷በአንጻሩ የእስራኤል ጦር በራፋ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.