Fana: At a Speed of Life!

በኦታዋ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦታዋ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በወንዶች ማራቶን ሌንጮ ተስፋዬ ርቀቱን 2 ሰዓት 12 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆኗል፡፡

ሌላኛው አትሌት አዳሙ ጌታሁን ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቋል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች ማራቶን ማረጓ ሃየሎም ርቀቱን 2 ሰዓት 32 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፋለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.