Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻዲሊ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻዲሊ ሀሰን የቡልድግሉ ወረዳን ከሰዳል ወረዳ የሚያገናኝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

አቶ አሻዲሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መንግስት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው።

የሁለቱን ወረዳ ቀበሌዎች የሚያገናኘው የመንገድ መሰረተ ልማት የወረዳዎቹ ህዝቦች ለዘመናት የቆየው የእርስ በርስ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያግዛል ብለዋል።

የሰዳል ወረዳ በተፈጥሮ የታደለች ወረዳ በመሆኗ ያለውን እምቅ ተፈጥሮ ሃብት በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

በወረዳዎቹ ባለፉት ዓመታት ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በርካታ የልማት ሥራዎች እንዳይከናወኑ ችግሮች እንደነበረ ጠቁመው÷አሁን በተገኘው ሠላም ከስጋት ወጥቶ ፊትን ወደ ልማት ማዞር ይገባል ነው ያሉት።

ህብረተሰቡ አሁን የተገኘውን ሠላም በዘላቂነት በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ፍሬ የማፍራት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መናገራቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የክልሉ መንግስት ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የሚደረገው የማሟያ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ አጋዥ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.