Fana: At a Speed of Life!

የሌማት ትሩፋት አርሶ አደሩ የልማት አቅሙን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠቀም ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) (ኢ/ር) በዳውሮ ዞን የሌማት ትሩፋት ውጤቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በዞኑ ኢሠራ ወረዳ በሌማት ትሩፋት ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች የተሻሻለ ዝሪያ ያሏቸው ላሞች በማርባት በኑሯቸው ተጨባጭ ለውጦች ማስመዝገብ መቻላቸውን አንስተዋል።

የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም በአካባቢያቸው የሚገኙ ተፈጥሮ ሃብቶችን አቀናጅተው በትብብር እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረላቸውም ተናግረዋል።

ውጤቱን ይበልጥ ለማስፋፋት የሚያግዙ ዝሪያ ማሻሻያ ግብዓቶችንና ተከታታይ ድጋፎችን መንግስት አጠናክሮ እንዲቀጥል አርሶ አደሮቹ ጠይቀዋል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) (ኢ/ር) በበኩላቸው÷በወረዳዎቹ የተመለከቷቸው የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ የሆኑ ጅምሮች የተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው ያለውን እምቅ ሃብትና ጉልበት እንዲሁም ጊዜያቸውን አቀናጅተው እንዲጠቀሙ የሌማት ትሩፋት ሥራው ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረላቸው መመልከታቸውን አስረድተዋል።

ብልጽግናን ለማረጋገጥ በየደረጃው እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ መሪዎችና ህብረተሰቡ በትብብር መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

በዞኑ ከተለያዪ አካባቢዎች የሚቀርቡ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት መንግስት አቅም የፈቀደውን ሁሉ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡ ትብብርና ተሳትፎ ሊጎለብት እንደሚገባ ከህዝብ ጋር ባካሄዱት የጋራ ወይይት ላይ ማሰባሰባቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዞኑ ቶጫ፣ ከጪ እና ኢሠራ ወረዳዎች በተደረገው የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ጉብኝት ም/ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት፣ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.