Fana: At a Speed of Life!

ሳውዝ ሃምፕተን ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በድጋሚ ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ሳውዝ ሃምፕተን በዓለማችን ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኘውን የፍጻሜ ጨዋታ በማሸነፍ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከአንድ የውድድር ዓመት በኋላ በድጋሚ መመለሱን አረጋግጧል።

ዛሬ 11 ሰዓት ጀምሮ በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም ወደፕሪሚየር ሊጉ የሚያድገውን 3ኛ ክለብ ለመለየት በተካሔደው የእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፕ የጥሎ ማለፍ ፍጻሜ ጨዋታ ሳውዝ ሃምፕተኖች ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አሮን አርምስትሮንግ ለሳውዝ ሃምፕተን አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎም ሳውዝ ሃምፕተን ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዳግም መመለሱን አረጋግጧል።

ከሳውዝ ሃምፕተን በተጨማሪ ሌስተር ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ቀደም ሲል ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጋቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.