Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የሴክተር ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሴክተር ጉባዔ የ3ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መድረኩ ባለፈው የሴክተር ጉባዔ ያስቀመጥነውን አቅጣጫ በመገምገም ቀሪ ተግባራት የምናሟላበት ነው ብለዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኡመድ ኡጁሉ በበኩላቸው÷ የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት አገልግሎት የተቀናጀ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ ለማድረግ ሚኒስቴሩ አበረታች ሥራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጉባዔው ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈ ቤት ተወካዮች፣ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ መሥተዳድሮች የተውጣጡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.