Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ፓኪስታን የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ፓኪስታን የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በፎረሙ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡

በተጨማሪም የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃና አርአያ ስላሴ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያጠናክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.