Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሦስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።

በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡድኖች ጋር ተጋርተዋል።

ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሦስት የውድድር ትራኮች ተከፋፍሎ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በውድድሩ ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስቴሩ የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎውን በማሳደግ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ÷ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.