Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ባለፉት 10 ወራት ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሃይሉ ጉዱራ እንደገለጹት÷ በክልሉ ለመሰብሰብ የታቀደውን ከ13 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ከማሳካትና የክልሉን ገቢ ከማሳደግ አንፃር የሚሰሩ ቀሪ ሥራዎች አሉ።

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት የተሰበሰበው ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።

ይህም ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ ታክስ ነክ ካልሆነ ገቢ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል።

ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር መዘርጋቱ፣ ውዝፍ እዳዎችን አሟጦ መሰብሰቡ እንዲሁም የቅሬታ አፈታት ሥርዓት በመሻሻሉ ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በ40 ግብር ከፋዮች ፋይል ላይ በተደረገ የማጣራት ስራ በ29ኙ ላይ ከግብር ሕግ ተገዥነት አንፃር ጥሰት እንደተገኘ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.