Fana: At a Speed of Life!

ለ67 ዓመታት በበረራ አስተናጋጅነት ያገለገሉት ቤቲ ናሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) በአሜሪካ አየር መንገድ ለ67 ዓመታት በበረራ አስተናጋጅነት በማገልገል የክብረ ወሰን ባለቤት የነበሩት ቤቲ ናሽ በ88 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡

አየር መንገዱ እንዳስታወቀው÷ ቤቲ ናሽ የተባሉት ግለሰቧ በአሜሪካ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ 1957 ጀምሮ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ለሰባት አስርት ዓመታት በሚጠጋ አገልገሎት ጊዜ ደንበኞቻችንን በመንከባከብ ያሳለፉት ቤቲ ናሽ ህልፈተ ህይወት አየር መንገዱ ማዘኑን ገልጿል።

በአሜሪካ የበረራ አስተናጋጆች ማህበር (APFA) በተመሳሳይ በበረራ አስተናጋጇ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ፤ ቤቲ ናሽ ላለፉት ስራቸውን በታታሪነት ሲወጡ እንደነበር ጠቅሷል።

ከአሜሪካ አየር መንገድ ይፋዊ በሆነ መንገድ በጡረታ ያልተሰናበቱት ቤቲ ናሽ፤ በልዩ ክትትል ህክምና ሲደረግላቸው እንደነበር ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ቤቲ ናሽ በአውሮፓያኑ 2022 መጀመሪያ ላይ በበረራ አስተናጋጅነት ለረጀም ጊዜ በማገልገል የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ሽልማት ማሸነፋቸወም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.