Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ሕዝብን መብትና ጥቅም ማስከበር የጋራ አጀንዳችን ነው – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር እየተወያዩ ነው።

አቶ አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት÷ በኢትዮጵያ ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ሌሎች አማራጮችን የመጠቀም ልምድ እንደነበር ጠቁመዋል።

አሁን የተፈጠረው አውድ እና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚደረጉ ውይይቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

“የአማራን ሕዝብ መብት እና ጥቅም ማስከበር የጋራ አጀንዳችን ነው” ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ÷ የክልሉን ሉዓላዊነት ማስከበር ሌላው የጋራ አጀንዳ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

አብሮ ለመሥራት የሚያስገድዱ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸው÷ በጋራ የሚደረጉ ውይይቶች ወሳኝ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ የጋራ ም/ቤት ሰብሣቢ ተስፋሁን ዓለምነህ÷ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መተማመን እና ሰላምን መሠረት ያደረገ ግንኙነት እንዲኖር የጋራ ምክር ቤቱ መመሥረቱን ገልጸዋል።

ለሰላም ግንባታ እና መረጋጋት ውይይት እና ድርድርን ማስፋት እንደሚገባና አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰላማዊ ውይይቶችን ማድረግ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

የፖለቲካ ጥያቄ አለኝ የሚል አካል ውይይትን መቀበል አለበት ያሉት ሰብሳቢው÷ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ማሰብ እና መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማኅበራዊ ፍትሕ መሟገት እንደሚገባቸው እና ፖለቲካ አቅም፣ አቋም እና ተሻጋሪነትን እንደሚጠይቅ አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.